ትራምፕ የተኩስ አቁም ስምምነት ይፋ ቢያደርጉም ሩሲያ በዩክሬን የኢነርጂ ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷ ተገለጸ

በምዕራብ ዩክሬን የኢነርጂ እና የባቡር መሠረተ ልማቶች ዒላማ መደረጋቸውም ተገልጿል
የምስሉ መግለጫ, በምዕራብ ዩክሬን የኢነርጂ እና የባቡር መሠረተ ልማቶች ዒላማ መደረጋቸውም ተገልጿል
ታትሟል
የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

ሩሲያ ስድስት የዩክሬን የኢነርጂ ተቋማት ላይ ጥቃት ማድረሷን ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ተናገሩ።

ዜሌንስኪ ይህንን ያሉት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ በዩክሬን እና ሩሲያ መካከል የኢነርጂ የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ተደርሷል ካሉ ከሰዓታት በኋላ ነው።

ያለፈው እሑድ ትራምፕ ባደረጉት ንግግር፤ ሁለቱ አገራት "የነዳጅ ማደያ፣ የኢነርጂ መሠረተ ልማት እና ሌሎች ተቋማት ላይ" ጥቃት ከማድረስ ይቆጠባሉ ብለው ነበር።

ሩሲያ በኃይል አቅርቦት መስመር ላይ ጥቃት ከፈጸመች በኋላ በኢዙይም ግዛት መብራት መጥፋቱን የዩክሬን ብሔራዊ ጣቢያ ዘግቧል።

በምዕራብ ዩክሬን የኢነርጂ እና የባቡር መሠረተ ልማቶች ዒላማ መደረጋቸውም ተገልጿል።

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቭሮቭ፤ ዩክሬን የተኩስ አቁም የሚያመጣው "ጥቅም አይገባትም" ብለዋል።

በተለያዩ የዓለም ክፍሎች ባሉ ግጭቶች ምክንያት ዓለም አቀፍ የነዳጅ ዋጋ ንሯል።

አሜሪካ የአጋማሽ ዘመን ምርጫ እየተቃረበ ሲሆን ከሩሲያ ናፍጣ የማስገባት ዕቅድ እንዳለ ትራምፕ አስታውቀዋል።

Skip podcast promotion and continue reading
BBC News Amharic የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናላችንን ይቀላቀሉ!
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

የዩክሬን የኃይል አቅርቦት ተቋም ዩክሬንርጎ እንዳለው፤ ሩሲያ ባደረሰችው ጥቃት ሳቢያ በካሪክቭ፣ ዶንቴስክ እና ዛፖሪዛዚሀ የኃይል መቆራረጥ አጋጥሟል።

በዩክሬን አንዳንድ አካባቢዎች መብራት በፈረቃ እየቀረበ ይገኛል።

ዜሌንስኪ በኤክስ ገጻቸው "ሩሲያ የኢነርጂ የተኩስ አቁም ለመቀበል ፈቃደኛ አለመሆኗን ያሳያል" ብለዋል።

የኪቭ ከንቲቫ ቪታል ኪልታሽኮ በቴሌግራም ገጻቸው እንዳስታወቁት፤ ባለ 25 ፎቅ ሕንጻ በድሮን ተመትቶ አንድ ሰው ሲገደል፣ 11 ሰዎች ተጎድተዋል።

ትራምፕ የተኩስ አቁሙን ይፋ ሲያደርጉ ዜሌንስኪ ጉዳዩ "ለእኔ አዲስ ዜና ነው" ብለው ነበር።

ሆኖም "አሜሪካውያን የእውነት ሩሲያ የተኩስ አቁሙን እንድታከብር ማድረግ ከቻሉ" የተኩስ አቁሙ ጦርነቱን ለማቆም "ትልቅ እርምጃ" መሆኑን ተናግረዋል።

ትራምፕ ጦርነቱ "አውዳሚ" እንደሆነ በመግለጽ የኢነርጂ የተኩስ አቁሙን አስፈላጊነት አስምረውበታል።

ሞስኮ በበኩሏ ዒላማ ያደረገቻቸው ሥፍራዎች የዩክሬንን ወታደራዊ እንቅስቃሴ የሚደግፉ መሆናቸውን ገልጻለች።

ከዚህ በፊት ዩክሬን በሩሲያ የምታደርው ጥቃት ሞስኮ "ጦርነቱን በፋይናንስ የምትደግፍበትን አቅም ለማዳከም ያለመ" መሆኑን አስታውቃለች።

የቢቢሲ መረጃ ማጣሪያ 'ቢቢሲ ቬሪፋይ' ሁለቱም አገራት የሚያደርሱት ጥቃት ቀዝቃዛ ወራት ከመጀመራቸው በፊት ተባብሶ መቀጠሉን ያሳያል።

በአውሮፓውያኑ 2016 በሩሲያ የነዳጅ እና ጋዝ ተቋማት ላይ 273 ጥቃቶች ተመዝግበዋል። ይህም ከቀደመው ዓመት በ124 ይበልጣል።

በዓለም አቀፍ ደረጃ ግጭቶችን የሚከታተለው አክሌድ ሩሲያ በዩክሬን የኢነርጂ መሠረተ ልማት ላይ የምታደርሰው ጥቀት 2.4 በመቶ መሆኑን ይፋ አድርጓል።

ዓለም አቀፍ የነዳጅ ገበያ ላይ የተፈጠረውን ቀውስ ለመቀልበስ ሩሲያ ነዳጅ ማቅረብ እንድትችል፣ ዩክሬን በሞስኮ የነዳጅ ፋብሪካዎች ላይ ጥቃት ማድረስ እንድታቆም ትራምፕ አሳስበዋል።

አሜሪካ በጊዜያዊነት ሩሲያ ላይ የተጣለውን የነዳጅ ሽያጭ ማዕቀብ የምታነሳ ከሆነ ለፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን "ስጦታ" እንደሚሆን ፕሬዝንት ዜሌንስከሊ ተናግረዋል።