ጃፓን ላጋጠማት ከባድ ሙቀት አዲስ ስም አወጣች

የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

ጃፓን 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እና ከዚያም በላይ ሆኖ ለሚያቃጥለው ሐሩር የበጋ ወር አዲስ ስም አውጥታለች።

ጃፓን እጅግ የከፋ ነው የተባለውን የበጋ ወቅት ተከትሎ የተከሰተውን ከፍተኛ ሙቀት "ኮኩሾቦ' ስትል ጠርታዋለቸ።

ትርጉሙ "በጭቃኔ የሚያነድ ሙቀት'፣ 'የከፋ ሙቀት'፣ ወይንም 'ከባድ ሙቀት' ተብሎ እንደሚተረጎም የጃፓን እና የዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

አዲሱ ስያሜ በኦንላየን ዘንድ ከፍተኛ ተቀባይነት ያገኘ ሲሆን " በጣም ከፍተኛ ሞቃት ቀን" የሚለው ደግሞ በሁለተኛነት በርካቶች የሚጠቀሙት ቃል ሆኗል።

በመላው ዓለም ከፍተኛ ሙቀት ወይንም የሙቀት ማዕበል እየተለመደ የመጣ ሲሆን እነዚህም በሰው ልጆች ከከርሰ ምድር በሚወጣ የነዳጅ ዘይት አጠቃቀም ላይ የተመሰረተ ነው።

የጃፓን ሚቲዎሮሎጂ ኤጀንሲ አርብ ዕለት መጠቀም የጀመረው ይህ አዲስ መጠሪያ፣ ኮኩ (koku) የሚል ቃል ይዞ ነበር።

ይህም የሙቀቱን መጠን ለመግለጽ ከባድ ወይንም ጨካኝ የሚል ትርጉም አለው።

ጃፓናውያን ያጋጠማቸውን ከባድ ሙቀት ለመግለጽ የትኛውን ቃል እንደሚመርጡት ለማወቅ 13 አማራጮች ቀርበውላቸው ነበር።

478,000 አስተያየታቸውን በሰጡበት በዚህ የዳሰሳ ትናት በዋነናነት የተመረጠው "ኮኩሾቦ' ሆኗል።

በጃፓን ከ25፣ ከ30 እንዲሁም ከ35 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ ለሆኑ ሞቃታማ ቀናት የየራሳቸው ስያሜ አላቸው።

አዲሱ ቃል ጃፓን ከባለፈው ዓመት ወዲህ ላጋጠማት ሐሩር ለሆነው የአየር ጠባይ የተሰጠ ነው።

በጃፓን እአአ የ2025 በጋ ወራት እአአ 1898 ወዲህ ከፍተኛ ሙቀት የተመዘገበበት ነው።

በሰኔ እና በነሐሴ የሙቀት መጠኑ 40 ዲግሪ ሴንቲግሬድ እና ከዚያ በላይ እንደሚደርስ ተገምቷል።