የአዲስን እናንሳ ፎቶግራፍ ፌስቲቫል አሸናፈዎች

በጋራ መኖሪያ ቤቶች መሃል የሚያልፍ አስፋል ላይ እናትና ልጅ ሲሻገሩ።
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል
ታትሟል

የአዲስ አበባን ነባራዊ ገጽታ መመዝገብን አላማው ያደረገ "ካፕቸር አዲስ" ወይም አዲስን እናንሳ የፎቶግራፍ ፌስቲቫል በሦስት ዘርፍ ሦስት ፎቶግራፎች ተመርጠው ፎቶ አንሺዎቹ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።

በፌስቲቫሉ ላይ በመሳተፍ እነዚህን ድንቅ የተባሉ ፎቶግራፎች ለመመልከት እድሉን ላላገኛችሁ የፎቶግራፍ አድናቂዎች ቢቢሲ አማርኛ አነሆ የተመረጡትን አቅርቧል።

አንደኛ ምድብ፡ የፎቶግራፍ ባለሙያዎች

አንድ መንገደኛ ዉሃ ባቆረ መንገድ ሲሻገር የሚያሳይ ፎቶግራፍ።
የምስሉ መግለጫ, የፎቶግራፍ ባለሙያዎች ምድብ አሸናፊ ከሆነው የአማኑኤል ፀጋዬ ስብስብ አንዱ ፎቶግራፍ።

በፎቶግራፍ ባለሙያዎች ምድብ ውስጥ የተካተቱ ምርጥ ፎቶግራፎች።

የቆሻሻ ክምር የሚያፀዱ ሰራተኞች የሚያሳይ ምስል።
የምስሉ መግለጫ, "አያስፈልገንም ብለን በጣልነው እዚህ ህይወት ይቀጠልበታል..."
በሥርዓት የተደረደሩ በርሜሎች እና ጀሪካኖችን ከአንድ ሰራተኛ ጋር የሚያሳይ ምስል።
የምስሉ መግለጫ, በርሜል ተራ
በሚያምር መልኩ የተደረደሩ ፍራፍሬዎች
የምስሉ መግለጫ, አትክልት ተራ

ሁለተኛ ምድብ፡ የሁሉም ነዋሪዎች ውድድር

በጋራ መኖሪያ ቤቶች መሃል የሚያልፍ አስፋል ላይ እናትና ልጅ ሲሻገሩ።
የምስሉ መግለጫ, በአዲስ አበባ ከሚገኙ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መካከል

ከሁሉም ነዋሪዎች ውድድር ምድብ ውስጥ ከተካተቱት ምርጥ ፎቶግራፎች መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል።

የአዲስ አበባ ቀላል ባቡር በወጋገን ባንክ አዲስ ቅርንጫፍ በኩል ሲያልፍ የሚያሳይ ምስል።
ከፒያሳ አትክልት ተራ አንድ ሰው አትክልት ተሸክሞ ሲሄድ። ከሩቅ ሜክሲኮ ላይ የሚሰሩተ አዳዲስ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች ይታያሉ።
የምስሉ መግለጫ, ጎመን ነጋዴው
ሰዎች በተለምዶ ቅጥቅጥ የህዝብ ማመላለሻ የሚባለው መኪና ላይ እቃ ሲጭኑ።
የምስሉ መግለጫ, አውቶብስ ተራ

ሶስተኛ ምድብ፡ የዲፕሎማቶች ውድድር

በምሽት አንዲት ባለሱቅ በትክክል ከተደረደሩ የሱቁ ሸቀጦች ጋር የሚያሳይ ምስል።
የምስሉ መግለጫ, በዲፕሎማቶች ምድብ አሸናፊ ከሆነው ጄፍ ሌ ካርዲት ስብስብ አንዱ የሆነው ፎቶግራፍ።

በዲፕሎማቶች ምድብ ውስጥ ከተካተቱት ምርጥ ፎቶግራፎች መካከል የሚከተሉት ተጠቃሽ ናቸው።

አዲስ አበባን በስፋት የሚያሳይ ምስል ሲሆን ከአዲስ አበባ ስቴዲየም ጀምሮ የከተማው መውጫ መልክአምድር የሚያሳይ ምስል።
የምስሉ መግለጫ, አዲስ አበባ ስታዲየምና ባሻገር
አንድ አህያ ከከተማ ታክሲ አጠገብ ቆማ የሚያሳይ ምስል።
የምስሉ መግለጫ, ተራ ጥበቃ