ቀጥታ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘገበ

ከሁለት ሳምንት በፊት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተኮሰችው ፀረ መርከብ ክሩዝ ሚሳዔል ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት መመታታቸውን አሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ሦስት ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ዘገቡ። ዘገባው ባህረተኞቹ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ገልጾ በጭስ መታፈን እና በነበረ መንገጫገጭ ጭንቅላታቸው ላይ ተመትተው ራስ ምታት እንደነበራቸው አስታውቋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. የኢራን ልዑክ ወደ አሜሪካ የሄደው "ለሰላም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር" መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

    የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ

    የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤን ለመታደም ከፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ጋር ወደ አሜሪካ የተጓዙት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የኢራን ልዑክ ወደ ኒውዮርክ ያመራው "ለሰላም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር" ነው አሉ።

    ሚኒስትሩ አክለውም "ኢራን ለማንኛውም ጥቃት በጽናት ትቆማለች። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ለእውነተኛ ዲፕሎማሲም ዝግጁ ነን" ሲሉ ተናግረዋል።

    የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይህንን አስተያየት የሰጡት፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝን የባሕር ወሽመጥ ዳግም ለመክፈት ኢራን ያቀረበችውን ሀሳብ "አለመቀበላቸውን" ተከትሎ ነው።

    ፕሬዚዳንት ትራምፕ ዕቅዱን አለመቀበላቸው ከተሰማ በኋላ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከኢራን ጋር ተጨማሪ ውይይቶች እንደሚደረጉ መግለጻቸው ታውቋል።

    አራግቺ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እንደተናገሩት፣ አሜሪካ በኢራን የቀረበውን ዕቅድ ከተቀበለች የሆርሙዝ የባሕር መስመር በሰባት ቀናት ውስጥ ይከፈታል።

    የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከአሜሪካ ጋር ያለው ግጭት የሚገታው “በድርድር መፍትሔ ላይ ሲደረስ ብቻ” መሆኑን ተናግረው ነበር።።

    የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት የቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ ቀደም ሰኔ ወር ላይ በኢራን እና አሜሪካ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ላይ ካሉ ቅድመ ሁኔታዎች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

  2. ኢራን በሆርሙዝ ላይ በፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘገበ

    ነዳጅ ጫኝ መርከብ

    ከሁለት ሳምንት በፊት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተኮሰችው ጸረ መርከብ ክሩዝ ሚሳዔል ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት መመታታቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ሦስት ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ዘገቡ።

    ዘገባው ባሕረተኞቹ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ገልጾ በጭስ መታፈን እና በነበረ መንገጫገጭ ጭንቅላታቸው ላይ ተመትተው ራስ ምታት እንደነበራቸው አስታውቋል።

    ከስምንቱ ባሕረተኞች መካከል አንዱ ከፍተኛ መኮንን ሲሆን ቀሪዎቹ ግን ተራ አባላት መሆናቸውን ዘገባዎቹ ጨምረው አመልክተዋል።

    ስምንቱም ከአደጋው በኋላ ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸው ተገልጿል።

    የኢራን ሚሳዔል የነበሩበትን መርከብ ባጠቃበት ወቅት መርከበኞቹ ወደ ግዳጅ የተሰማራ ጦር አባላት ሆነው በሥፍራው መገኘታቸውን ተጠቅሷል።

    ባለሥልጣናቱ መርከቡ የአሜሪካ ንብረት አለመሆኑን ገልጸው፣ የባሕር ኃይል መርከብ ነች በማለት ብቻ የማን እንደሆነች ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

    በየካቲት ወር ከኢራን ጋር የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ የቆሰሉ እና የተገደሉ የአሜሪካ ወታደሮችን ቁጥር በመሰነድ እና በማሳወቅ ረገድ ለውጦች ሲደረጉ በመቆየታቸው ፔንታጎን ስለጉዳት መጠኑ በሚቀርቡ ጥያቄዎች እና ትችቶች ጫና ውስጥ ወድቋል።

    እስከ ረቡዕ ዕለት ድረስ፣ የፔንታጎን የጦሩ ጉዳት ትንተና ሥርዓት በግጭቱ ምክንያት 861 የአሜሪካ ወታደሮች ጉዳት እንደደረሰባቸው መዝግቦ ነበር።

    እነዚህ ስምንት የባሕር ኃይል አባላት በመረጃ ቋቱ ውስጥ የተካተቱት እአአ ከመስከረም 14ቱ ጥቃት በኋላ 10 ቀናት ካለፈ በኋላ ነበር።

    የአሜሪካ ባለሥልጣን ሪፖርቱ የዘገየበት ምክንያት ጉዳቶች ወይም ምልክቶች ከጊዜ በኋላ ሊታዩ መቻላቸውን እና ሥርዓቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ወዲያውኑ የማዘመን አቅም ስለሌለው መሆኑን ተናግረዋል።