የኢራን እና አሜሪካ አደራዳሪዎች ውይይቱ ይቀጥላል ብለው እንደሚጠብቁ ተዘገበ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የኢራን እና አሜሪካ አደራዳሪዎች ዛሬ ወይም ነገ ከሁለቱ አገራት ጋር በተናጠል ውይይት ይካሄዳል ብለው እንደሚጠብቁ ሮይተርስ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮችን ጠቅሶ ዘገበ።
የኳታር አሸማጋዮች እና የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ለተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባዔ ኒው ዮርክ ይገኛሉ።
የኢራኑ ኢርና የዜና ወኪል ኒው ዮርክ ለሚገኘው የልዑካን ቡድን ቅርብ የሆኑ ምንጮችን ጠቅሶ ከዚህ ቀደም እንደዘገበው ከሆነ ከአሜሪካ ጋር ድርድር ለማድረግ ፍላጎት የላቸውም። አራግቺ ነገ ወደ ኢራን እንደሚመለሱን ተዘግቧል።
“የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ ዕይታ እና አቋም በኳታር አሸማጋዮች በኩል ለአሜሪካ በግልጽ ቀርቧል። ኢራን ምላሹን እየጠበቀች ነው” ሲሉም ምንጩ ተናግረዋል።
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ከኢራን በኩል የቀረበውን በሰባት ቀናት ውስጥ የሆርሙዝ ወሽመጥን የመክፈት ዕቅድን ውድቅ ቢያደርጉም፤ ድርድር በቅርቡ ይቀጥላል ብለው ተስፋ እንደሚያደርጉ ትናንት ተናግረዋል።





