ቀጥታ, ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘገበ

ከሁለት ሳምንት በፊት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተኮሰችው ፀረ መርከብ ክሩዝ ሚሳዔል ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት መመታታቸውን አሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ሦስት ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ዘገቡ። ዘገባው ባህረተኞቹ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ገልጾ በጭስ መታፈን እና በነበረ መንገጫገጭ ጭንቅላታቸው ላይ ተመትተው ራስ ምታት እንደነበራቸው አስታውቋል።

ጭምቅ ሃሳብ

የቀጥታ ሽፋን

  1. ሽመልስ አብዲሳ በድጋሚ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ሆነው ተመረጡ

    የኦሮሚያ ክልል ፕሬዚደንት ሽመልስ አብዲሳ

    የኦሮሚያን ክልል ምክር ቤት አቶ ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አድርጎ በድጋሚ መረጠ።

    የክልሉ የሕዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት ዛሬ ሰኞ፣ መስከረም 18 / 2019 ዓ.ም በአዳማ እያካሄደ ባለው 7ኛው ጠቅላላ ጉባዔ ላላፉት ሰባት ዓመታት ክልሉን ሲያስተዳድሩ የነበሩትን ሽመልስ አብዲሳን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አድርጎ በዲጋሚ ሾሟል።

    አቶ ሽመልስ ምክር ቤቱ ሚያዚያ ወር 2011 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ተደርገው ከተሾሙ በኋላ ነበር በ2014 ዓ.ም ወደ ፕሬዚደንትነት የመጡት።

    የ40 ዓመቱ ሽመልስ አብዲሳ በፍልስፍና እና በሰብዓዊ መብቶች ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው።

    በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ የተመረጡት የምክር ቤቱ አባላት አቶ አብዱሰላም ዋሪዮንም የምክር ቤቱ አፈ ጉባዔ አድርጎ በአብላጫ ድምጽ መርጧል። አቶ አብዱሰላም ከወረዳ ጀምሮ እስከ ዞን ድረስ በተለያዩ ኃላፊነቶች ላይ አገልግለዋል።

    ምክር ቤቱ በዛሬው ውሎው የክልሉን አዲስ መንግሥት ያዋቅራል፣ የቋሚ አባላት ኮሚቴ ሹመቶችን፣ የተለያዩ ተቋማት ኃላፊዎችን ሹመቶች እንዲሁም ረቂቅ አዋጆችን ጨምሮ 10 አጀንዳዎችን ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል።

  2. በካናዳ ከጤና ተቋማት ሰራተኞች እና ህሙማን ስርቆት ስትፈፅም የነበረች ሴት ተከሰሰች

    የተሰረቁ ቁሳቁሶች
    የምስሉ መግለጫ, ፖሊስ ከተጠርጣሪዋ እጅ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ይዟል

    በካናዳ ኦንታሪዮ ግዛት ከተለያዩ ሆስፒታሎች የህሙማንን እና ሰራተኞችን ንብረት ስትሰርቅ የነበረች ሴት ላይ ክስ መመስረቱን ፖሊስ አስታወቀ።

    በግለሰቧ ላይ ማጭበርበር እና ስርቆትን ጨምሮ 65 የወንጀል ድርጊቶች ክስ ተመስርቶባታል።

    የኦንታሪዮ ግዛት ፖሊስ ተጠርጣሪዋ ከቶሮንቶ 56 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ የምትገኘው የበርሊንግተን ከተማ ነዋሪ የሆነችው የ34 ዓመቷ ናሲም ኢሮን እንደሆነች በስም ለይቷል።

    ፖሊስ ለቢቢሲ በላከው መግለጫው "ምርመራው የተጀመረው በህሙማንን እና በጤና ተቋማት ሰራተኞች ላይ ስርቆት እና ማጭበርበር መፈፀሙን የተመለከቱ በርካታ ጥቆማዎች ከደረሱት በኋላ" መሆኑን ገልጿል።

    በክስተቱ ላይ ምርመራ የተጀመረው እአአ የካቲት 2024 ሲሆን እስካለፈው ወር ድረስ ምርመራው ሲካሄድ ቆይቷል። በዚህም በርካታ የግለሰቦች ንብረቶችን እንደያዘ አስታውቋል።

    ተጠርጣሪዋ በግዛቷ በጤና ማዕከላት ውስጥ ትሰራ እንደነበርም መግለጫው አመልክቷል።

    ሆኖም በሆስፒታሎቹ ውስጥ በምን የሥራ ኃላፊነት ላይ ትሰራ እንደነበር ግልጽ አይደለም።

    ፖሊስ በምርመራው በአምስት የጤና ተቋማት ድርጊቶቹ መፈፀማቸውን ያረጋገጠ ሲሆን በሌሎችም ተፈፅሞ ሊሆን እንደሚችል በመግለጽ የተመሳሳይ ድርጊት ሰላባ የሆኑ ሰዎች ሊኖሩ ስለሚችሉ እንዲያሳውቁ አሳስቧል።

    ፖሊስ እንደገለጸው ከሆነ ተጠርጣሪዋ ከ5 ሺህ ዶላር በታች የሚሆኑ 44 የማጭበርበር፣ ከ5 ሺህ ዶላር በታች የሚገመቱ 13 የስርቆት እና የፍር ድቤት ትዕዛዝን ባለማክበር ሰባት ክሶች ተመስርተውባታል።

    ሌሎቹ ክሶች ደግሞ እምነትን ማጉደል እና ማስመሰልን የሚያካትቱ ናቸው።

  3. የኢራን ልዑክ ወደ አሜሪካ የሄደው "ለሰላም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር" መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ተናገሩ

    የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ

    የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤን ለመታደም ከፕሬዝዳንት ማሱድ ፔዜሽኪያን ጋር ወደ አሜሪካ የተጓዙት የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ለአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን የኢራን ልዑክ ወደ ኒውዮርክ ያመራው "ለሰላም ምቹ ሁኔታን ለመፍጠር" ነው አሉ።

    ሚኒስትሩ አክለውም "ኢራን ለማንኛውም ጥቃት በጽናት ትቆማለች። በተመሳሳይ ጊዜ፣ ለእውነተኛ ዲፕሎማሲም ዝግጁ ነን" ሲሉ ተናግረዋል።

    የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይህንን አስተያየት የሰጡት፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የሆርሙዝን የባሕር ወሽመጥ ዳግም ለመክፈት ኢራን ያቀረበችውን ሀሳብ "አለመቀበላቸውን" ተከትሎ ነው።

    ፕሬዚዳንት ትራምፕ ዕቅዱን አለመቀበላቸው ከተሰማ በኋላ በጥቂት ቀናት ውስጥ ከኢራን ጋር ተጨማሪ ውይይቶች እንደሚደረጉ መግለጻቸው ታውቋል።

    አራግቺ ባለፈው ሳምንት ሐሙስ እንደተናገሩት፣ አሜሪካ በኢራን የቀረበውን ዕቅድ ከተቀበለች የሆርሙዝ የባሕር መስመር በሰባት ቀናት ውስጥ ይከፈታል።

    የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ ከአሜሪካ ጋር ያለው ግጭት የሚገታው “በድርድር መፍትሔ ላይ ሲደረስ ብቻ” መሆኑን ተናግረው ነበር።።

    የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት የቀረቡት ቅድመ ሁኔታዎች ከዚህ ቀደም ሰኔ ወር ላይ በኢራን እና አሜሪካ መካከል በተፈረመው የመግባቢያ ሰነድ ላይ ካሉ ቅድመ ሁኔታዎች ጋር ተመሳሳይ መሆናቸውንም ተናግረዋል።

  4. ኢራን በሆርሙዝ ላይ በፈጸመችው የሚሳዔል ጥቃት ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት ጉዳት እንደደረሰባቸው ተዘገበ

    ነዳጅ ጫኝ መርከብ

    ከሁለት ሳምንት በፊት ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ በተኮሰችው ጸረ መርከብ ክሩዝ ሚሳዔል ስምንት የአሜሪካ ባሕር ኃይል አባላት መመታታቸውን የአሜሪካ መገናኛ ብዙኃን ሦስት ባለሥልጣናትን ጠቅሰው ዘገቡ።

    ዘገባው ባሕረተኞቹ ከባድ ጉዳት እንዳልደረሰባቸው ገልጾ በጭስ መታፈን እና በነበረ መንገጫገጭ ጭንቅላታቸው ላይ ተመትተው ራስ ምታት እንደነበራቸው አስታውቋል።

    ከስምንቱ ባሕረተኞች መካከል አንዱ ከፍተኛ መኮንን ሲሆን ቀሪዎቹ ግን ተራ አባላት መሆናቸውን ዘገባዎቹ ጨምረው አመልክተዋል።

    ስምንቱም ከአደጋው በኋላ ወደ መደበኛ ሥራቸው መመለሳቸው ተገልጿል።

    የኢራን ሚሳዔል የነበሩበትን መርከብ ባጠቃበት ወቅት መርከበኞቹ ወደ ግዳጅ የተሰማራ ጦር አባላት ሆነው በሥፍራው መገኘታቸውን ተጠቅሷል።

    ባለሥልጣናቱ መርከቡ የአሜሪካ ንብረት አለመሆኑን ገልጸው፣ የባሕር ኃይል መርከብ ነች በማለት ብቻ የማን እንደሆነች ለመናገር ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀርተዋል።

    በየካቲት ወር ከኢራን ጋር የተጀመረውን ጦርነት ተከትሎ የቆሰሉ እና የተገደሉ የአሜሪካ ወታደሮችን ቁጥር በመሰነድ እና በማሳወቅ ረገድ ለውጦች ሲደረጉ በመቆየታቸው ፔንታጎን ስለጉዳት መጠኑ በሚቀርቡ ጥያቄዎች እና ትችቶች ጫና ውስጥ ወድቋል።

    እስከ ረቡዕ ዕለት ድረስ፣ የፔንታጎን የጦሩ ጉዳት ትንተና ሥርዓት በግጭቱ ምክንያት 861 የአሜሪካ ወታደሮች ጉዳት እንደደረሰባቸው መዝግቦ ነበር።

    እነዚህ ስምንት የባሕር ኃይል አባላት በመረጃ ቋቱ ውስጥ የተካተቱት እአአ ከመስከረም 14ቱ ጥቃት በኋላ 10 ቀናት ካለፈ በኋላ ነበር።

    የአሜሪካ ባለሥልጣን ሪፖርቱ የዘገየበት ምክንያት ጉዳቶች ወይም ምልክቶች ከጊዜ በኋላ ሊታዩ መቻላቸውን እና ሥርዓቱ ወቅታዊ መረጃዎችን ወዲያውኑ የማዘመን አቅም ስለሌለው መሆኑን ተናግረዋል።