በለንደን ለተቃውሞ አደባባይ የወጡ ከ500 በላይ የ'ፓላስታይን አክሽን' ደጋፊዎች ታሰሩ

የፓላስታይን አክሽን ሰልፈኞች

የፎቶው ባለመብት, EPA

የንባብ ጊዜ: 2 ደቂቃ

ፓላስታይን አክሽን ላይ የተጣለውን እገዳን በመቃወም በማዕከላዊ ለንደን በተካሄደው ሰልፍ ላይ የተሳተፉ ከ500 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን የሜትሮፖሊሰታን ፖሊስ አስታወቀ።

የታሰሩት ሰዎች ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 87 እንደሚደርስም ፖሊስ ገልጿል።

በትራፋልጋር አደባባይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ተሰብስበው ቡድኑ ቀደም ሲል ባዘጋጀው ተቃውሞዎች ላይ እንደታየው "የዘር ማጥፋት ዘመቻን እቃወማለሁ"፤ "ፓላስታይን አክሽንን እደግፋለሁ" የሚል ጽሑፍ ይዘው ነበር።

በዲፌንድ ኦን ጁሪስ የተጠራው የቅዳሜው ተቃውሞ፤ ኤቭሪዋን ዴይ (የሁሉም ቀን) ተብሎ የተሰየመ ሲሆን "በፓላስታይን አክሽን ላይ እገዳ ለመቃወም" የተጠራ መሆኑ ተነግሯል።

አንዳንድ ሰልፈኞች በበኩላቸው የተቃውሞ መብት እንዲጠበቅ እና ለአሜሪካ እና ለእስራኤል ያላቸውን ተቃውሞ አሳይተዋል።

መንግሥት በፀረ ሽብር ሕግ መሠረት የፓላስታይን አክሽንን መደገፍ በሐምሌ 2025 ሕገ ወጥ ተደረገ።

እገዳው በየካቲት ወር ሕገ ወጥ ነው ቢባልም ይግባኝ እስኪባል ድረስ እገዳው ባለበት ይቀጥላል።

የከፍተኛ ፍርድ ቤት የሰጠውን የእገዳ ውሳኔ ተከትሎ ፖሊስ ሰልፈኞችን የማሰራቸው ዕድል አነስተኛ መሆኑ ተገልጾ ነበር። ነገር ግን በመጋቢት ወር የከተማዋ ፖሊስ ፓሊስታይን አክሽንን በመደገፍ ሰልፈፍ የሚወጡትን ማሰር እንደሚቀጥል ተናግሯል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

የቅዳሜው ሰልፍ ከመካሄዱ በፊት ፖሊስ ማስጠንቀቂያ በማውጣት ሰዎች ተሳታፊ እንዳይሆኑ አሳስቧል።

"ተሳታፊ ሰዎች በሽብርተኝነት ሕግ መሰረት ወንጀል መሆኑን ማወቅ አለባቸው። እናም ሕጉ ከተጣሰ እርምጃ ከመውሰድ ወደኋላ አንልም" ሲሉ የለንደን የፖሊስ ባልደረባ ኮማንደር ክሌር ስማርት ተናግረዋል።

በሰልፉ ላይ የተገኙት አንዳንድ ሰዎች የእስር ማስጠንቀቂያውን ለመጣስ ፈቃደኛ መሆናቸውን ለቢቢሲ ኒውስ ተናግረዋል።

ከታሰሩት መካከል የሜሲቭ አክተር ባንድ መስራች የሆኑት ሮበርት ዴል ናጃ ይገኙበታል። ቀደም ሲል ለፒኤ ኒውስ እንደተናገሩት ሰልፉ ላይ ለመገኘት የወሰኑት ፖሊስ "ሰዎችን እንደገና ለማሰር መወሰኑ አስቂኝ" እንደሆነ ስላሰቡ ነው።

ከተያዙ በትክክለኛው አካሄድ ፍርድ ቤት ቆሞ "ይህ ሕገወጥ እስራት ነው፣ ስለዚህ አልቀበለውም" ብሎ መከራከር እንደሚችሉ እርግጠኛ እንደሆኑ ተናግረዋል።

ሌላኛዋ ሰልፈኛ ሊንዳ ዎከር ወደ ሰልፉ ለመምጣት የወሰኑት "ባለፉት ሁለት ተኩል ዓመታት የዘር ማጥፋት ዘመቻ እየተካሄደ ነው" በመሆኑ እንደሆነ ጠቁመዋል።

"[መንግስት] እርምጃ ለመውሰድ ፈቃደኛ የሆነው ለማስቆም የሚሞክሩትን ሰዎች ብቻ ነው" ብለዋል።

እስራኤል በጋዛ የፈጸመችው ድርጊት የዘር ማጥፋት እንዳልሆነ በተደጋጋሚ የካደች ሲሆን ራስን የመከላከል ትክክለኛ መንገድ እንደሆነ ተናግራለች።

ሌላኛዋ ተቃዋሚ ለቢቢሲ እንደተናገረችው ከዚህ በፊት 10 ጊዜ የታሰረች ሲሆን አሁንም ተመሳሳይ ውጤት ትጠብቃለች።

በቀኑ 10፡50 ሰዓት ላይ የሜትሮፖሊታን ፖሊስ 212 ሰዎችን እንደታሰሩ እና "ሰዎች ለተከለከለ ድርጅት ድጋፍ እያሳዩ በመሆናቸው" እንደሚቀጥል ገልጿል።

ምሽት 5፡07 ሰዓት ላይ 523 ሰዎች መታሰራቸውን ተናግሯል። "በሙያቸው ለተሳተፉት ሁሉ ምስጋናችንን እናቀርባለን" ሲል ፖሊስ ተናግሯል።

የአገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ዪቬት ኩፐር ፓላስታይን አክሽን ከታገደበት ጊዜ ጀምሮ ቡድኑን በመደገፍ አደባባይ የወጡ ከ2 ሺህ 200 በላይ ሰዎች መታሰራቸውን አስታውቀዋል።