ቀጥታ, ኢራን ስምምነቱ ከተጣሰ “ከፍተኛ እርምጃ” እንደምትወስድ አስታወቀች

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ “ስምምነቱን በጣሰው በዛኛው ወገን ላይ ከፍተኛ እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ አስጠነቀቁ።

ጭምቅ ሃሳብ

ኢራን ስምምነቱ ከተጣሰ "ከፍተኛ እርምጃ" እንደምትወስድ አስታወቀች

የቀጥታ ሽፋን

ኢራን ስምምነቱ ከተጣሰ “ከፍተኛ እርምጃ” እንደምትወስድ አስታወቀች

አባስ አራግቺ

የፎቶው ባለመብት, AFP

የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አባስ አራግቺ “ስምምነቱን በጣሰው በዛኛው ወገን ላይ ከፍተኛ እርምጃ እንወስዳለን” ሲሉ አስጠነቀቁ።

ከኢራቅ ፕሬዝዳንት ናዚር አሚዲ ጋር የተወያዩት አራግቺ “በአሜሪካ እና በጽዮናዊው አስተዳደር አንዳንድ መግባቢያዎች መጣሳቸው ሰላም እና መረጋጋት በቀጣናው እንዳይሰፍን ከፍተኛ መሰናክል ይሆናል” ብለዋል።

የስምምነቱ “በተለይ የመጀመሪያው አንቀጽ” መጣስ ሰላም እና መረጋጋትን እንደሚያውክ ገልጸዋል።

“የመግባቢያ ሰነዱን በጥሩ መንፈስ እና ለስምምነቱ ታማኝ በመሆን መተግበር እንፈልጋለን” ብለዋል።

ሆኖም ግን ስምምነቱ “በዚያኛው ወገን ከተጣሰ ከፍተኛ እርምጃ እንወስዳለን” በማለት አስጠንቅቀዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ በኢራን የሆርሙዝ ወሽመጥ አስተዳደር ውስጥ ማንኛውም ጣልቃ ገብነት ውጥረቱን እንደሚያባብስ መናገራቸውም ይታወሳል።

በሆርሙዝ ወሽመጥ በኩል እያለፈ የነበረ በፓናማ የተመዘገበ መርከብ ትናንት ቅዳሜ ጥቃት ከደረሰበት በኋላ አሜሪካ በኢራን ላይ ጥቃት ፈጽማለች።

የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ በአጸፋ ምላሽ በኩዌት እና ባሕሬን በሚገኙ የአሜሪካ መሠረተ ልማቶች ላይ የድሮን እና ሚሳዔል ጥቃቶች ማድረሱን ገልጿል።

ኩዌት እና ባሕሬን በኢራን የደረሰባቸውን ጥቃት አውግዘዋል።