የደቡብ አፍሪካው የመብት ታጋይ የሊቀ ጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ ህይወት በምስሎች

ታትሟል

ሊቀ ጳጳስ አቡነ ዴዝሞን ቱቱ በደቡብ አፍሪካ ውስጥ ነበረውን የዘር መድልኦ ሥርዓት በመታገል በኩል በነበራቸው ሚና በዓለም ዙሪያ ታላቅ አክብሮትን አትርፈዋል።

በ90 ዓመት እድሜያቸው እሁድ ዕለት ከዚህ ዓለም በሞት የተለዩትን የኖቤል የሰላም ተሸላሚውን የዴዝሞን ቱቱን ህይወት መለስ ብለው በጥቂቱ የሚያሳዩ ፎቶ ግራፎችን እነሆ፡

በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች አገዛዝን በመቃወም ሰላማዊ ትግል በመካሄዳቸው በአውሮፓውያ በ1984 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል
የምስሉ መግለጫ, በደቡብ አፍሪካ የጥቂት ነጮች አገዛዝን በመቃወም ሰላማዊ ትግል በመካሄዳቸው በአውሮፓውያ በ1984 የኖቤል የሰላም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል
ቱቱ የኬፕ ታውን ሊቀ ጳጳስ ሆነው በተሾሙበት ወቅት በ1986 (እአአ) ከባለቤታቸው ሌያህ ጋር
የምስሉ መግለጫ, ቱቱ የኬፕ ታውን ሊቀ ጳጳስ ሆነው በተሾሙበት ወቅት በ1986 (እአአ) ከባለቤታቸው ሌያህ ጋር
ቱቱ የኬፕ ታውን የመጀመሪያው ጥቁር ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኋላ የጥቁሮች መኖሪያ አካባቢዎችን ሲጎበኙ 1990 (እአአ)
የምስሉ መግለጫ, ቱቱ የኬፕ ታውን የመጀመሪያው ጥቁር ሊቀ ጳጳስ ሆነው ከተሾሙ በኋላ የጥቁሮች መኖሪያ አካባቢዎችን ሲጎበኙ 1990 (እአአ)
በ1993 (እአአ) የአፓርታይድ ሥርዓትን እንዲያበቃ በማድረጋቸው ኔልሰን ማንዴላ እና ፍሬድሪክ ዴክላርክ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሲቀበሉ ቱቱ በቴሌቪዥን እየተመለከቱ ሲያጨበጭቡ
የምስሉ መግለጫ, በ1993 (እአአ) የአፓርታይድ ሥርዓትን እንዲያበቃ በማድረጋቸው ኔልሰን ማንዴላ እና ፍሬድሪክ ዴክላርክ የኖቤል የሰላም ሽልማትን ሲቀበሉ ቱቱ በቴሌቪዥን እየተመለከቱ ሲያጨበጭቡ
ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ ኬፕ ታውን ውስጥ ከንግሥት ኤልዛቤት እና ከፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ጋር በ1995 (እአአ)
የምስሉ መግለጫ, ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ ኬፕ ታውን ውስጥ ከንግሥት ኤልዛቤት እና ከፕሬዝዳንት ኔልሰን ማንዴላ ጋር በ1995 (እአአ)
ለንደን ውስጥ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የአፓርታይድ ሥርዓት ያበቃበት 10ኛ ዓመት በ2004 (እአአ) ሲከበር ንግግር ሲያደርጉ
የምስሉ መግለጫ, ለንደን ውስጥ ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የአፓርታይድ ሥርዓት ያበቃበት 10ኛ ዓመት በ2004 (እአአ) ሲከበር ንግግር ሲያደርጉ
ቱቱ 80 ዓመታቸው ላይ የግለታሪክ መጽሐፋቸው በተመረቀበት ጊዜ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ሲደንሱ፣ 2011 (እአአ)
የምስሉ መግለጫ, ቱቱ 80 ዓመታቸው ላይ የግለታሪክ መጽሐፋቸው በተመረቀበት ጊዜ በሥነ ሥርዓቱ ላይ ሲደንሱ፣ 2011 (እአአ)
ኔልሰን ማንዴላ ጓደኛ የነበሩት ቱቱ በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ንግግር ሲያደርጉ ስሜታዊ ሆነው ነበር በ2013 (እአአ)
የምስሉ መግለጫ, የኔልሰን ማንዴላ ጓደኛ የነበሩት ቱቱ በቀብር ሥነ ሥርዓታቸው ላይ ንግግር ሲያደርጉ ስሜታዊ ሆነው ነበር በ2013 (እአአ)
በ2013 (እአአ) የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማ ኬፕ ታውን ውስጥ የቱቱን የኤድስ መርጃ ማዕከል በጎበኙበት ወቅት
የምስሉ መግለጫ, በ2013 (እአአ) የወቅቱ የአሜሪካ ፕሬዝዳንት የነበሩት ባራክ ኦባማ ኬፕ ታውን ውስጥ የቱቱን የኤድስ መርጃ ማዕከል በጎበኙበት ወቅት
መንፈሳዊው መሪ ዳላይ ላማ በ2015 (እአአ) ሕንድ ውስጥ ልደታቸውን ባከበሩበት ጊዜ ኬክ ለዴዝሞን ቱቱ ሲሰጡ
የምስሉ መግለጫ, መንፈሳዊው መሪ ዳላይ ላማ በ2015 (እአአ) ሕንድ ውስጥ ልደታቸውን ባከበሩበት ጊዜ ኬክ ለዴዝሞን ቱቱ ሲሰጡ
ሊቀ ጳጳስ ቱቱ በ2019 (እአአ) የሰሴክስ አልጋ ወራሽ ሃሪና ባለቤቱን ሜጋንን ከልጃቸው ጋር ባገኙበት ጊዜ
የምስሉ መግለጫ, ሊቀ ጳጳስ ቱቱ በ2019 (እአአ) የሰሴክስ አልጋ ወራሽ ሃሪና ባለቤቱን ሜጋንን ከልጃቸው ጋር ባገኙበት ጊዜ
ሌያህ ቱቱ የባለቤታቸው ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ በዚህ ዓመት ጥቅምት 2021 (እአአ) ላይ 90ኛ ዓመታቸው በተከበረበት ሲደንሱ
የምስሉ መግለጫ, ሌያህ ቱቱ የባለቤታቸው ሊቀ ጳጳስ ዴዝሞን ቱቱ በዚህ ዓመት ጥቅምት 2021 (እአአ) ላይ 90ኛ ዓመታቸው በተከበረበት ሲደንሱ

ሁሉም ፎቶግራፎች የባለቤትንት መብታቸው በሕግ የተጠበቀ ነው።