የአፍሪካን ሳምንት በምስል፡ እሳትና በረዶ

ታትሟል

በዚህ ሳምንት ከተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት እና ከተለያዩ የዓለማችን ክፍሎች ከሚገኙ አፍሪካውያን የተሰበሰቡ ምርጥ ምስሎች

የኬኒያ የአክሮባት ቡድን አባላት በናይሮቢ እሳት የመትፋት ትርዒት ሲያቀርቡ
የምስሉ መግለጫ, የኬኒያ የአክሮባት ቡድን አባላት በናይሮቢ እሳት የመትፋት ትርዒት ሲያቀርቡ
ሁለት ወጣት የዳምቤ ቦክሰኞች በሌጎስ የጦረኞች ውድድር ላይ ሲቧቀሱ፤- ይህ ባሕላዊ ጨዋታ በሰሜን ናይጄሪያ የሐውሳ ጎሳ አባላት የሚዘወተር ነው።
የምስሉ መግለጫ, ሁለት ወጣት የዳምቤ ቦክሰኞች በሌጎስ የጦረኞች ውድድር ላይ ሲቧቀሱ፤- ይህ ባሕላዊ ጨዋታ በሰሜን ናይጄሪያ የሐውሳ ጎሳ አባላት የሚዘወተር ነው።
ኬኒያዊቷ ተዋናይት ሉፒታ ኒዮንጎ እሁድ ዕለት በተካሄደው የኦስካር ሽልማት ላይ ፀጉሯን በሩዋንዳ ባህላዊ አጊያጊያጥ አስውባ
የምስሉ መግለጫ, ኬኒያዊቷ ተዋናይት ሉፒታ ኒዮንጎ እሁድ ዕለት በተካሄደው የኦስካር ሽልማት ላይ ፀጉሯን በሩዋንዳ ባህላዊ አጊያጊያጥ አስውባ
የ43 ዓመቱ ሰይድ፣ ከማዕከላዊ ሞሮኮ 60 ኪሎ ሜትር ርቃ በምትገኘው አዚላል የበረዶ ግግር ላይ የተቀረቀረበትን መኪና ለማስለቀቅ ሲታገል
የምስሉ መግለጫ, በምዕራብ አውሮፓ የተከሰተው ወቅቱን ያልጠበቀው ቀዝቃዛ አየር በዚህ ሳምንት በሞሮኮው አትላስ ተራሮች ላይም በረዶ ፈጥሮ ነበር
የአድማ በታኝ ፖሊሶች በሴራሊዮን የተቃዋሚ ፓርቲ ደጋፊ የሆነውን ሰልፈኛ መሪት ለመሬት ሲጎትተው
የምስሉ መግለጫ, እረቡ እለት በሴራሊዮን የተደረገው ምርጫ በአንዳንድ ቦታዎች ከተደረጉ የተቃውሞ ሰልፎች ውጭ በቡዙ ቦታዎች ሰላማዊ ነበር
ምንም እንኳ በዚህ ሳምንት ሴራሊዮን ምርጫ ብታካሂድም እነዚህ ግለሰቦች ግን ከሚመጣው ፕሬዝዳንት አዲስ ነገር አይጠብቁም፤ ይልቅስ ጠንክረው ከወንዙ አሸዋ እና ጭቃ መካከል ወርቅ ለማግኘት ይፈልጋሉ
የምስሉ መግለጫ, እነዚህ ሴሪዮላውያን ከአሸዋ እና ጭቃ ወርቅ ለይቶ ለማውጣት ጠንክረው እየሠሩ ነው
በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ከሆሎት ስደተኞች ማቆያ ሲወጡ ለመታሰቢያ ፎቶ ሲነሱ
የምስሉ መግለጫ, በእስራኤል የሚገኙ ኤርትራውያን ስደተኞች ከሆሎት ስደተኞች ማቆያ ሲወጡ ለመታሰቢያ ፎቶ ሲነሱ

Images courtesy of AFP, Reuters, PA and Getty Images