ትራምፕ ዛሬ ስምምነት ይፈረማል ብለው ሲጠብቁ፤ ኢራን በቀጣይ ቀናትም ሊሆን እንደሚችል ጠቁማለች

የፎቶው ባለመብት, Bloomberg via Getty Images
የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዛሬ እሑድ ከኢራን ጋር ስምምነት ይፈረማል ብለው እየጠበቁ ነው። የኢራን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቃል አቀባይ ኢስማኤል ባጋይ ግን ስምምነቱ ዛሬ እንደማይፈረም እና በቀጣይ ቀናት ሊፈረም የሚችልበት ዕድል እንዳለ መናገራቸው ተዘግቧል።
የኢራን መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡት ቃል አቀባዩ ከአሜሪካ ጋር የተደረሰው “የመጨረሻ ስምምነት ሳይሆን ውዝግብ የሚያስነሱ ጉዳዮችን በተመለከተ አጠቃላይ አቅጣጫ ማስቀመጥ ነው” ብለዋል።
ስምምነቱ ዛሬ እሑድ ባይፈረምም እንኳን በቀጣይ ቀናት የመፈረም ዕድል እንዳለ አክለዋል።
የፓኪስታንጠቅላይ ሚኒስትር ሻሀባዝ ሻሪፍ ሁለቱ ወገኖች የመግባቢያ ሰነዱ ላይ እንደተስማሙ ገልጸዋል።
ፕሬዝዳንትዶናልድ ትራምፕም በ80ኛ ዓመት ልደታቸው ቀን ስምምነቱ እንደሚፈረም እየጠበቁ ነው።
ሁለቱን አገራት በዋናነት ያሸማገሉት ፓኪስታን እና ኳታርን ጨምሮ ሌሎች አገራትም ስምምነቱ ላይ ኤሌክትሮኒክ ፊርማቸውን ያኖራሉ ተብሎ ይጠበቃል።
በመግባቢያ ሰነዱ መሠረት የተኩስ አቁሙ ለ60 ቀናት ተራዝሞ ስለ ኢራን የኒውክሌር መርሃ ግብር ድርድር ይጀመራል ተብሏል።
ከአሸማጋዮቹአንዷ የሆነችው የኳታር ልዑካን ቴህራን የገቡ ሲሆን፤ ልዑካኑ በአሜሪካ እና ኢራን መካከል የመልዕክት ልውውጥን እያሳለጡ መሆኑም ተገልጿል።
ትራምፕ ስምምነቱ እንደተፈረመ በአፋጣኝ የሆርሙዝ ወሽመጥ ይከፈታል ብለዋል።




















